ከቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አክብረው በመመለስ ባሉ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰው ምንድን ነው? !
#Ethiopia | “ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ፤ ደማቸውንም ስለእግዚአብሔር አፈሰሱ፤ ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሱ” ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
ወንድሞቻቻን የእውነት ምስክር (ሰማዕታት) ናችሁ
እንደውትሮው እነዚህ ከአቃቂ ባቡር ጣቢያ መገላ ሠፈር የተወጣጡት18 የሚሆኑት እህት እና ወንድሞቻችን በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ደረስው በዓለ ነግሡን ለማክበር የተቀጣጠሩት ማልደው ነበር። ስእለት ያለው ስለቱን ለማድረስ፤ ቅዱስ ገብርኤል በምልጃው እንዲደርስለት የሚሳለውም ስእለቱን ለመሳል ጓጉተው ቀኑን ሲጠብቁ ነበር።
የሚጓዙበት ቀን ደርሶ ጎዞ ወደ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ይሆናል። ወደ ገዳሙ በጉዞ ላይ እያሉ የሰው አውሬ ይገጥማችዋል። የሚጓዙበትን አይሱዙ መኪና አስቁመው በመሳሪያ በማስፈራራት 10 ሞባይል እና 30 ሺህ ብር በመውሰድ ይለቋቸዋል። እነዚህ ወንድሞቻችንም ጥቂት እንደተጓዙ የጸጥታ አካላት አግኝተው የገጠማቸውን ዝርፊያ ያስረዱና ለጓጉለት እና ለወራት በናፍቆት ወደ ጠበቁት ገዳም ጉዞ ይቀጥላሉ።
ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምም ይደርሳሉ። ክብረ በዓሉ ላይ ተሳትፈው፤ የተሳለው ስእለቱን አድርሶ፤ የሚሳለውም ተስእሎ፤ ታላቁ መላእክ ለከርሞ በሰላም እንዲያደርሳቸውና ስእለታቸውን እንደቀበላቸው ተማጽነው እንደወትሮ በአንድነት እንደወጡት በአንድነት ለመመለስ በመጡበት መኪና ላይ ተሳፍረው ጉዞ ወደ አቃቂ ይሆናል። (እዚህ ላይ 18 ሆነው ከተጓዙት መካከል ሁለቱ በሌላ መኪና እንደተመለሱ ልብ ይሏል)
እናም የሰማዕታት ወንድሞቻችንን ሕይወት የቀጠፈ ክስተት የተፈጠረው በመልስ ጉዞው ወቅት ነበር።
አይ ይሄ ጥቁር ቀን!!!
ወንድሞቻችን እግዚአብሔርን በመዝሙር እያመሰገኑ እየተጓዙ እያሉ ከምሽቱ 5:00 ገደማ አዋሽን አልፎ በመተሀራ አቅራቢያ ለገበንቲ በሚባል አካባቢ ሲደርሱ ከፊታቸው በፍጥነት በመጓዝ ላይ በነበረው ታታ የሕዝብ አውቶብስ ላይ የተኩስ ሩምታ ይከፈታል። ታታውም የተኩሱን ሩምታ በፍጥነት እንዳለፈ ወንድሞቻችንን የያዘው መኪና ግን የተኩሱን ሩምታ ሳያልፍ የተተኮሰው ጥይት አራት ወንድሞቻችንን ሲገድል፤ ሁለት እህቶቻችንን እጅና እግር ላይ ያቆስላል።
በሕይወት የተረፉትን ወንዶችና ሁለት ሴት ልጆች የያዙት አረመኔዎችም ወደ ጫካ ይገባሉ። ሴቶቹ አንዷ እጇ ላይ የተመታች ስለነበረና አንዷም በፍጥነት ከነሱ ጋር መጓዝ ስላልቻለች ሁለቱን ሴቶች ይለቋቸውና ወንዶቹን ይዘው ይሰወራሉ።
ሴቶቹም ከእገታው ተመልሰው መኪናው ወደ ተመታበት ቦታ ሲደርሱ ሚኪናው በጥይት ተመትተው ከተገደሉት አራት ሰማዕታት ወንድሞቻችን ጋር በእሳት ተያይዞ ያገኙታል። እህቶቻችንም አንድም በድንጋጤ፣ አንድም በድካም እና በአቅም ማጣት እሳቱን ማጥፋት ሳይችሉ የወንድሞቻቸው አስክሬን በእሳት ሲባላ ሲያዩ ራሳቸውን ይስታሉ።
እነዛን እህቶች ከኋላ ሲመጡ የነበሩ ሌሎች ተጓዞች ይዘው ወደ ሆስፒታል ይወሰዳሉ። መረጃው ከሞላ ጎደል ይሄ ነው። አብዛኛውን መረጃ ያገኘነው ከሟች ቤተሰቦች ሲሆን፤ የሟች ቤተሰቦችም መረጃውን ያገኙት በሕይወት ከተረፉትእህቶች ነው።
አሁን ታጋቾቹን አስመልክቶ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አጋቾች የታጋቾቹን ቤተሰቦች ገንዘብ በመጠየቅ ላይ መሆናቸው ነው።
ለታጋቾች ቤተሰቦች ሲባል ስለ ጉዳዬ ከዚህ በላይ ምንም ማለት አይቻልም። ወደ ፊት ትክክለኛውን መረጃ ከቤተሰብ እየጠየቅን የምናቀርብ ይሆናል። የአቃቂ በሰቃ ሕዝብ የሟቾቹንም (የሰማዕታቱን) ሆነ የታጋቾቹን ቤተሰቦች በማጽናናት ረገድ እያደረገ ያለው ሥራ የሚያስመሰግን ሲሆን፤ ቤተሰቦችን በማቋቋም ሆነ የታጋች ቤተሰቦችን በሁሉ ነገር በመደገፍ እገዛ ማድረግ ያስፈልገናል።
የአቃቂ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነትም ቤተሰቦቹን በማጽናናት ልዩ ልዩ የወንጌል መርሐ ግብር ማድረግ ይገባታል።
በሕይወት ያጣናቸው ሰማዕታት ወንድሞቻችን ማናቸው?
🎯 አዲሱ ሁንዴቻ
አዲሱ ሁንዴቻ ረዥም ዘመኑን ከስፖርት ጋር ያሳልፈ በቅርቡም በቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ተከናውኖ በነበረው የክረምት ውድድር ላይ ዋንጫ ያገኘው የአቃቂ ወንድማማቾች ጤና ስፖርት ማኅበር መስራች አባል እና የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ነበር ። አዲሱ ከዚህ በተጨማሪም በሚያሽከረው መለስተኛ የጭነት መኪና ራሱንና ቤተሰቦቹን ያስተዳድራል።
🎯 ቴድሮስ ነዲ [ እንጪኔ ]
ቴድሮስ ነዲ [ እንጪኔ ] የአይሱዙ መኪና ባለቤት ና በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ስድስት በሹፍርና እያገለገለ የሚገኝ ወንድም የነበር ነው ።
🎯 ደሳለኝ ደሜ [ ቦቼ ]
ወንድማችን ደሳለኝ ደሜ (ቦቼ) 18ንቱን ወንድሞች አሳፍሮ ገዳም ያደረሰው አይሱዚ መኪና ባለቤት ሲሆን፤ ቦቼ ቤተሰቦቹን በአረመኔዎቹ በወደመው መኪና ያስተዳድር ነበር።
🎯 አወቀ ገኖ
አወቀ ገኖ ነው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አቃቂ ቅርንጫፍ ቄራ የእንሰሳት እርድ ክፍል ኃላፊ ሆኖ ሲያገለገል የነበረ ወንድማችን ነው ።